የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የውስጥ ኦዲት
የስራ ዘርፉ ሃላፊ ሙሉ ስም፡- ሙሉእመቤት ፀጋው ስልክ፡- 0921310350
የስራ ዘርፉ የሰው ሃይል ብዛት፡- 1
ጾታ፡- ሴ
የትምህርት ደረጃ ፡- ዲግሪ
- የስራ ልምድ ፡- 6ዓመት ከ6ወር
የስራ ዘርፉ ዋና ዋና ተግባራት
- ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራትን ከመስሪያ ቤቱ አላማ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የስጋት ተጋላጭነት ያለባቸውን የስራ ክፍሎች መሰረት ያደረገ እቅድ በማዘጋጀት ለመ/ቤቱ ሃላፊ አቅርቦ በማኔጅመንት እንዲፀድቅ ማድረግ
- የፀደቀውን እቅድ ለሚመለከተው አካል መላክ
- እቅዱን ሁሉም ኦዲት ተደራጊ የስራ ክፍሎች እንዲያውቁት ማድረግ
- አስቀድሞ ብቅድ ያልተያዘ ልዩ ኦዲት እንዲደረግ በመ/ቤቱ የበላይ ሃላፊ ሲታዘዝ ኦዲት ማድረግ
- የፋይናንስ አጠቃቀሙ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን የጠበቀ መሆኑን በፋይናንሻል ኦዲት ያረጋግጣል
- የተቋሙንንብርት አያያዝና አጠቃቀምመንግስት ባወጣው አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት በትክክል ተፈጣሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የንብርት ኦዲት ያደርጋል
- በውስጥ ኦዲት የተከናወኑ ተግባርትን የሚገልፅ ወቅታዊና አመታዊየስራ አፈጻጸምሪፖርት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ሃለፊ ማቅረብ
- በምርመራ ወቅት ለተደረሰባቸው ግኝቶችመተማመኛ የዘጋጃል፣ከተመርማሪዎች ጋር የፈራረማል
- መተማመኛ በማይፈርሙ ተመርማሪዎች ላይሪፖርት በማዘጋጀትለቅርብ ሃላፊው ያቀርባል ውሳኔውንም የከታተላል በበጀት አመቱ መጨረሻ
- በተደረሰባቸው ግኝቶች ላይ ከቅርብ ሃላፊው ጋር ይወያያል
- በበጀት አመቱ መጨረሻ በመስሪያ ቤቱ አማካኝነትየተደረገውን ቆጠራ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረትመከናወኑን በማረጋገጥከቆጠራ ሰነዱ ጋር ለቢሮው እንዲቀርብ ማድረግ ፣ይህንንም ለማረጋገጥ በቆጠራ ወቅት በታዛቢነት መገኘት
- የውጭ ኦዲተሮጭ በሚያቀርቧቸው ግኝቶች ላይየእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ክትትል ማድረግ
- የኦዲት መግቢያና መውጫ ውይይት ላይ በመገኘት አስፈላጊውን ማብራሪያ ማድረግ